Norges billigste bøker

Bøker av Alex Abreham

Filter
Filter
Sorter etterSorter Populære
  • av Alex Abreham
    204,-

    አሌክስ አብርሃም "እናት - ፍቅር - ሀገር" በሚል ርዕስ ባሳተመው የግጥም መጽሐፍ ውስጥ 36 ያህል ረጃጅም ግጥሞች አሉ፡፡ መጽሐፉ ከሽፋኑ ጀምሮ ትርጉም አለው፤ ጣዕም አለው፡፡ ... ቃላቱ ሸጋ፣ ሙዚቃውም ቆንጆ የሚባል ነው፡፡ የሀሳቦቹም ክንፎች ነጠላ አይደሉም፣ የሚመስጡ ቁምነገሮች፣ የሚያስደምሙ እይታዎች አሉባቸው፡፡ ከሁሉ ይልቅ አይጐረብጡም፡፡ ቀላል ይመስላሉ፣ ግን ውብ ናቸው፡፡ በተለይ በሳሳው ጐናችን በኩል ጠቃሚ ነገር አላቸው፡፡የቋንቋው ውበት ድንቅ ነው፡፡ ደረጀ በላይነህበአዲስ አድማስ ጋዜጣ

  • av Alex Abreham
    204,-

    "አንፈርስም አንታደስም" የደራሲ አሌክስ አብርሃም ሁለተኛ የግጥም መፅሐፍ ነው። መፅሐፉ ውስጥ የተካተቱት ግጥሞች ከስነፅሁፍ ውበታቸው ባለፈ የትውልዱን ጩኸት የሚያስተጋቡ ፣ አንዴ ካነበቧቸው ከአእምሮ የማይጠፉ ህያው ሐሳቦች ናቸው። የደራሲ አሌክስ አብርሃም ግጥሞች በሬዲዮ ፕሮግራሞች ፣ በስነፅሁፍ መድረኮች፣ በተለያዩ አንባቢያን ከመቅረባቸውም በላይ በመነባነብ ፣ እንዲሁም በአንድ ሰው ተውኔት ስልት ተዘጋጅተው ከፍ ያለ አድናቆት ተችሯቸዋል። ደራሲ አሌክስ አብርሃም አጭር ልብወለዶች መፃፍ ከመጀመሩ በፊት በርካታ ግጥሞቹን በሬዲዮ በማቅረብ ይታወቃል።

  • av Alex Abreham
    253,-

    ዶክተር አሸብር እና ሌሎችም በደራሲ አሌክስ አብርሃም የተፃፈ የአጭር እና መካከለኛ ልቦለድ ስብስቦች መፅሐፍ ነው። ይህ የኢትዯጵያዊያንን ማህበራዊ ጉዳይ በጥልቀት የሚዳስስ የልብ ወለድ እና ወግ መፅሐፍ ደራሲውን ከአንባቢዎቹ ጋር በመፅሐፍ ደረጃ ያስተዋወቀ የመጀመሪያ የህትመት ስራው ነው። አሌክስ አብርሃም ባለፉት አስራ ሶስት ዓመታት በኢትዮጵያ ስነፅሁፍ ደምቆ የታየ ገጣሚ፣ የአጭር እና ረዥም ልብወለድ እንዲሁም የወግ ፀሐፊ ሲሆን፤ ከዛ በፊት በመሃበራዊ ድረ ገፅ በሚፅፋቸው ወጎች ፣ ጠንካራ ማህበራዊ ሂሶች እና ረዣዥም ግጥሞቹ በብዙ ሚሊየን አንባቢዎች ዘንድ ከፍተኛ እውቅና ያተረፈ ወጣት ደራሲ ነው። ደራሲው በአገር ውስጥ ይታተሙ በነበሩ የተለያዩ መፅሔቶች ላይ አምደኛ ሁኖ ከመስራቱም በላይ ስራዎቹ በብዛት በሬዲዮ፣በዩቲዩብ ተተርከው ከፍተኛ ተቀባይነት ለማግኘት በቅተዋል። በፊልም የተቀናበረ አንድ ስራውም ተወዳጅ ለመሆን በቅቷል። ዶክተር አሸብር እና ሌሎችም እንዲሁም ከዛ በኋላ ደራሲው ያሳተማቸው አምስት መፅሐፍት ባለፉት አስርት አመታት ውስጥ በአማርኛ ተፅፈው ከፍተኛ ሽያጭ ካስመዘገቡ በጣት የሚቆጠሩ መፅሐፍት ተርታ ለመመደብ በቅተዋል፣ መፅሐፉ በታተመት ዓመት በሬዲዮ በተደረገ የአንባቢዎች ምርጫ የዓመቱ ምርጥ መፅሐፍ ተብሎ ለመመረጥ የበቃ መፅሃፍ ሲሆን በቀጣዩ ዓመትም የደራሲው ሌላኛ መፅሐፍ የዓመቱ ምርጥ መፅሐፍ ሁኖ ለመመረጥ በቅቷል። እነሆ ይህ መፅሐፍ በመላው ዓለም ለሚኖሩ አንባቢዎች በአማዞን በኩል ለገበያ ቀርቧል። መልካም ንባብ።

  • av Alex Abreham
    335,-

    ፍቅር ሁሉ ፍቅር አይደለም። በደፈናው አፈቀርን ወይም ተፈቀርን እንበል እንጅ ሰዎች ምናችንን በምን ምክንያት እንደወደዱልን በእርግጠኝነት መናገር የሚቻል ነገር አይደለም። ሰዎች ከማንነት በላይ ለአካላዊ ውበት በፍቅር ሊወድቁ ይችላሉ፤ ምናልባትም ይህ ለራሳቸውም አይገባቸውም ይሆናል። ከነጭራሹ ወደድናችሁ ያሉን ሰዎች እንደወደዱን ማረጋገጫችንስ ምንድነው ? ትዳር ? ስጦታ? ቃልኪዳን? ለእኛ የሚከፍሉት መስዋዕትነት? በመኖር ብቻ የሚመለስ ጥያቄ ሳይሆን አይቀርም። በዚህ መፅሐፍ ከነመኖራቸው ትዝ የማይሉን ጥቃቅን ስሜቶች ስንጥቃቸው እየሰፋ ሕይዎትን ለከባድ ምስቅልቅል ሲዳርጉ እናያለን። ምናለበት ተብለው ችላ የተባሉ እንደውም እንደበጎ ነገር የሚታዩ ጉዳዮች በጥልቀት ሲቃኙ ያላቸውን አደገኛ ስር እንመለከታለን። በሕይዎት ውስጥ ቁጭ ብለን የሰቀልነውን ቁመን ማውረድ ሲያቅተን ሌሎች ድሎት ያሉት ነገር ለሌላው መከራ ሲሆኑ ፣ እንታዘባለን። ፅናት፣ ፍቅር ፣ ስደት ፣ናፍቆት ፣ዓላማ ፣ ሐዘን ፣ደስታ ፣ በውብ ትረካ ተሰድረው እናገኛቸዋለን። እንደቀላል የልጅነት ሁዳዳችን ላይ የተጣለች ቅንጣት የቃል ዘር በኋለኛው ዘመናችን ዛፍ ሁና ጥላዋን በአኗኗራችን ላይ ስታጠላ እንታዘባለን። በመጨረሻም መፅሐፉን ስንከድን የራሳችንን ሕይወት ከፍተን መመልከት እንጀምራለን። ደራሲ አሌክስ አብርሃም በማህበራዊ ድረገፆች ፣ በመፅሔቶች በሚፅፋቸው በሁሉም ስራዎቹ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘ ወጣት ደራሲ ነው። ከዚህ በፊት ዶ/ር አሸብርና ሌሎችም ፣ እናት ፍቅር ሐገር፣ ዙቤይዳ ፣ አንፈርስም አንታደስም ፣ ከዕለታት ግማሽ ቀን እንዲሁም ይህ አልተዘዋወረችም የሚል ስራው ተጠቃሽ ናቸው። መልካም ንባብ።

Gjør som tusenvis av andre bokelskere

Abonner på vårt nyhetsbrev og få rabatter og inspirasjon til din neste leseopplevelse.