Utvidet returrett til 31. januar 2024

Bøker utgitt av Hezon Academy

Filter
Filter
Sorter etterSorter Populære
  •  
    345,-

    በዚህ መጽሐፍ በዋነኛነት የምንመለከተው የኒውተንን የሥነስበት ሥነሥፍራዊ ትንተና ነው። ለዚሁ መንደርደሪያ እንዲሆን ሥነ-እንቅስቃሴን እና የሥነ-ፈለክ ሊቃውንት ከጥንት ጀመሮ የፕላኔቶችን እንቅስቃሴ ለመቀመር ያደርጓቸውን ሐተታዎች እና የቀመሯቸውን መተንብዮች በመጀመሪያዎቹ ሁለት ምዕራፎች ቀንጭበን እንመለከታለን። ሦስተኛው ምዕራፍ የኒውተንን የሥነስበት ሥነሥፍራዊ ትንተና ይዟል። ምዕራፉ ቀደምት የግሪክ የሥነሥፍራ ምሁራን ያበለጸጓቸውን ስለሚጠቀም አንባቢው ጸሐፊው በሥነቁጥር እና በሥነሥፍራ ላይ ያሳተመውን መጽሐፍ (አንተነህ ብሩ, 2023) ቀድሞ እንዲያነብ ይመከራል። ምዕራፍ አራት የኒውተንን የስበት ቀመር በአመች መልኩ ለማስቀመጥ የሚጠቅሙ ሒሳባዊ ሐረጎችን ባጭሩ ይዳስሳል። ምዕራፍ አምስት በኒውተን የስበት ቀመር ውስጥ የስበት ያዊት ን ለመወሰን ሄነሪ ካቨንዲሽ የተባለ እንግሊዛዊ የተፈጥሮ ተመራማሪ እና ፈላስፋ ያበለጸገውን የጥምዘት ሚዛን አሠራር እና ሥነስሌት ይዟል። በመጨረሻው ምዕራፍ የኒውተን የስበት ንድፈ ሐሳብ ጉድለቶችን ባጭሩ ያቀርባል።

  • av Anteneh Biru Tsegaye
    271,-

    በዚህ መጽሐፍ ልሙድ ሥነ-እንቅስቃሴን ወይም ኒውተናዊ ሥነ-እንቅስቃሴ የሚባለውን ቀንጭበን እንመለከታለን። መጽሐፉ አራት ምዕራፎች አሉት። በመጀመሪያው ምዕራፍ በቦታ እና በጊዜ ላይ በተለያዩ አሳብያን የተደረጉ ሐተታዎች ቀርበዋል። በሁለተኛው ምዕራፍ እስከ ኒውተን ዘመን የነበረውን ሐተታ እንቅስቃሴ ባጭሩ ቀርቧል ፣ ምዕራፉ የኒውተንን ሦስት መሰረታዊ የእንቅስቃሴ ሕግጋት ድንጋጌዎችን በማቅረብ ይቋጫል። ምዕራፍ ሦስት የልሙድ ሥነ እንቅስቃሴን ሒሳባዊ ሐተታ ያቀርባል ፤ በምዕራፉ አስፈላጊ ብይኖች ፣ የእንቅስቃሴ ዐይነቶች እና ሒሳባዊ ስሌቶቻቸው ባጭሩ ቀርበዋል። የመጨረሻው ምዕራፍ የኒውተንን የእንቅስቃሴ ሕግጋት በአመች ቅርጽ ለማስቀመጥ ከኒውተን በኋላ የተበለጸጉትን ላግራኝዣዊ እና ሐሚልተናዊ አቀራረቦችን ውልብታ ይዟል። መልካም ንባብ።

  • av Anteneh Biru Tsegaye
    270,-

    መጽሓፉ ሦስት መዕራፎች አሉት። በመጀመሪያው ምዕራፍ ስለ ቁጥሮች እና መሰረታዊ ስሌቶች ቀርበዋል። በሁለተኛው ምዕራፍ የሥነ-ንጽጽር ቅቡሎች እና ይሁንታዎች በቁንጽል ቀርበዋል። በሦስተኛው ምዕራፍ ዩክሊዳዊ ሥነ-ሥፍራ መሰረታዊ ብይኖች ፣ ይሁንታዎች ፣ አዋጆችን ከነ ማረጋገጫቸው ቀርበዋል። ዘዌዎች ፣ ተማሳይነት ፣ የፓይታጎረስ አዋጅ ፣ ክፍላተ ቅንብባት ከብዙ አዋጆች እና ማረጋገጫ ጋር ተመርጠው ቀርበዋል። የሥነ-ሥፍራ ድርሰቱ የተመረጠው ከቀደምት የግሪክ የሥነ-ሥፍራ ሊቃውንት ድርሰቶች በመሆኑ በዘመናዊ (ትንተናዊ ፣ ካርተሳዊ) ሥነ-ሥፍራ የተቃኘ አንባቢ ከመሰረታዊ ድንጋጌዎች ጀምሮ እያንዳንዱን አዋጅ በርጋታ ማየት ይኖርበታል።

Gjør som tusenvis av andre bokelskere

Abonner på vårt nyhetsbrev og få rabatter og inspirasjon til din neste leseopplevelse.